የክረምት ዝማሪ (ከኗሪ አንደበት)
*
*
*
ሰማይ_
ፍቅር መስራት አምሮት
ካቧራማ መሬት
የናፍቆቱን ግለት ጠል አወረደባት
*
በሁለቱ ሩካቤ በፍቅራቸው እቶን
ትኩስ ያፈር ጠረን ኗሪዎቿን ሸቶን
በጠረኑ ሰክረን
እንዲህ እንላለን
<ሰማይ ሆይ ተዋሰብ ከምድሪቱ ጋራ
በተራክቧችሁ ነው ህይወት የምንዘራ>
*
*
*
(ኤልሳ ሙሉጌታ)
*
*
*
ሰማይ_
ፍቅር መስራት አምሮት
ካቧራማ መሬት
የናፍቆቱን ግለት ጠል አወረደባት
*
በሁለቱ ሩካቤ በፍቅራቸው እቶን
ትኩስ ያፈር ጠረን ኗሪዎቿን ሸቶን
በጠረኑ ሰክረን
እንዲህ እንላለን
<ሰማይ ሆይ ተዋሰብ ከምድሪቱ ጋራ
በተራክቧችሁ ነው ህይወት የምንዘራ>
*
*
*
(ኤልሳ ሙሉጌታ)